ቀጥታ፡

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በመጠናቀቁ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 15/2018(ኢዜአ)፦ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በመጠናቀቁ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ከተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም ሁለቱ ወገኖች በቀጣናው ብሎም በዓለም አቀፍ የጋራ ጉዳዮች ላይ መክረዋል።

አንቶኒዮ ጉተሬዝ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ተጠናቅቆ በመመረቁ ኢትዮጵያውያን እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።

በተጨማሪም በቅርቡ ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ጉባዔን በስኬት ማስተናገዷን አስታውሰው፥ ለዚህም የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም