አሰልጣኝ ዮሴፍ ገብረወልድ ለሴቶች ብሄራዊ ቡድን የማጣሪያ ጨዋታ ዝግጅት ለ33 ተጫዋቾች ጥሪ አደረጉ - ኢዜአ አማርኛ
አሰልጣኝ ዮሴፍ ገብረወልድ ለሴቶች ብሄራዊ ቡድን የማጣሪያ ጨዋታ ዝግጅት ለ33 ተጫዋቾች ጥሪ አደረጉ
አዲስ አበባ፤ መስከረም 14/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ አሰልጣኝ ዮሴፍ ገብረወልድ ቡድኑ ከታንዛንያ ጋር ላለበት የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች ዝግጅት ለ31 ተጫዋቾች የመጀመሪያ ዙር ጥሪ አድርገዋል።
ብሄራዊ ቡድኑ በሞሮኮ አስተናጋጅነት እ.አ.አ በ2026 ለሚካሄደው 16ኛው የሴቶች አፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ ከታንዛንያ አቻው ጋር ጥቅምት 12 እና 18 ቀን 2018 ዓ.ም የመጨረሻ ዙር ወሳኝ ጨዋታዎቹን ያደርጋል።
የሉሲዎቹ ዋና አሰልጣኝ ዮሴፍ ገብረወልድ ለጨዋታታዎቹ ዝግጅት ከሀገር ውስጥ ክለቦች ለ31 ተጫዋቾች ጥሪ ማስተላለፋቸውን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።
ታሪኳ በርገና (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)፣ አበባ አጄቦ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)፣ ሮማን አምባዬ (ሸገር ከተማ) እና ቤተልሄም አምባዬ (መቻል) ጥሪ የተደረገላቸው ግብ ጠባቂዎች ናቸው።
ብዙዋየሁ ታደሰ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)፣ ታሪኳ ዴቢሶ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)፣ ትዕግስት አዳነ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)፣ ቅድስት ዘለቀ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)፣ እጸገነት ብዙነህ (መቻል)፣ ብርቄ አማረ (መቻል)፣ ሰናይት ሸጎ (መቻል)፣ ድርሻዬ መንዛ (መቻል) እና ለምለም አስታጥቄ (ሃዋሳ ከተማ) በተከላካይ መስመር ተካተዋል።
እመቤት አዲሱ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)፣ ዙፋን ደፈርሻ (ኢትዮ ኤሌክትሪክ)፣ ፀጋ ንጉሴ (ሃዋሳ ከተማ)፣ እፀገነት ግርማ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)፣ መሳይ ተመስገን (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)፣ ቤተልሄም መንተሎ (መቻል)፣ ገነት ኃይሉ (መቻል)፣ ጋብሪዬላ አበበ (ኢትዮ ኤሌክትሪክ)፣ ቤዛዊት ንጉሴ (መቻል) እና ስመኝ ምህረቴ (ሲዳማ ቡና) የአማካይ ተጫዋቾች ናቸው።
ሴናፍ ዋቁማ (መቻል)፣ እሙሽ ዳንኤል (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)፣ ምርቃት ፈለቀ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)፣ ንግስት በቀለ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)፣ ማህሌት ምትኩ (ኢትዮ ኤሌክትሪክ)፣ ዳግማዊት ሰለሞን (ኢትዮ ኤሌክትሪክ)፣ ቤተልሄም ታምሩ (ሸገር ከተማ) እና ሰላማዊት ጎሳዬ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ) በአጥቂ መስመር ቡድኑን እንዲቀላቀሉ ጥሪ ተደርጎላቸዋል።
በቀጣይ ከሀገር ውጪ ለሚጫወቱ ተጫዋቾች የዓለም አቀፉ እዝግር ኳስ ማህበር (ፊፋ) ኢንተርናሽናል ውድድር መስኮት መመርያን በጠበቀ መልኩ ጥሪ እንደሚደረግላቸው ፌዴሬሽኑ ገልጿል።
ተጫዋቾቹ ነገ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ሪፖርት እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።
ኢትዮጵያ በደርሶ መልስ ውጤት ካሸነፈች ለአፍሪካ ዋንጫ ማለፏን ታረጋግጣለች።
በሞሮኮ አስተናጋጅነት እ.አ.አ በ2026 በሚካሄደው 16ኛው የሴቶች አፍሪካ ዋንጫ 12 ሀገራት ይሳተፋሉ።