ሕዳሴ በሀገር ወዝ ተሞሽሮ ጉባ ላይ የቆመ የልማት ሐውልታችንና መቻላችን የተረጋገጠበት ሕዝባዊ ዐሻራ ነው - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ - ኢዜአ አማርኛ
ሕዳሴ በሀገር ወዝ ተሞሽሮ ጉባ ላይ የቆመ የልማት ሐውልታችንና መቻላችን የተረጋገጠበት ሕዝባዊ ዐሻራ ነው - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
አዲስ አበባ፤ መስከረም 13/2018(ኢዜአ)፦ ሕዳሴ በሀገር ወዝ ተሞሽሮ ጉባ ላይ የቆመ የልማት ሐውልታችንና መቻላችን የተረጋገጠበት ሕዝባዊ ዐሻራ ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው እንደገለጹት በፊቼ ጨምበላላ የዘመን ቆጠራ እውቀት እና ፍልስፍናው የሚታወቀው የሲዳማ ሕዝብ የሕዳሴን መጠናቀቅ ውብ በሆነው የቄጣላ ስርዓቱ ደምቆ በአደባባይ አክብሯል ብለዋል።
ሕዳሴ የዓባይን ወንዝ እራት እና መብራት ሆኖ የኢትዮጵያ ልጆችን የልማት ተስፋ እውን ሊያደርግ እንደ አድማስ ዐለት በጽናት እና በትብብር መንፈስ የቆመ የሕዝቦች እውነት እና ታሪክ ነው ሲሉም ገልጸዋል።
ዓባይን ከሺህ ዓመታት በኋላ ከሀገሩ ጋር ያስማማው የሕዳሴ ድል የሲዳማ ክልልንም የሀገራዊ የልማት እቅዶች በይቻላል መንፈስ እንዲሰራ ዕድል ይፈጥርለታል ነው ያሉት፡፡
ሕዳሴ በሀገር ወዝ ተሞሽሮ ጉባ ላይ የቆመ የልማት ሐውልታችንና መቻላችን የተረጋገጠበት ሕዝባዊ ዐሻራ ነው ብለዋል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው።