የካፈቾ የዘመን መለወጫ በዓል "ማሽቃሮ" በቦንጋ ከተማ እየተከበረ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የካፈቾ የዘመን መለወጫ በዓል "ማሽቃሮ" በቦንጋ ከተማ እየተከበረ ነው

ቦንጋ፤ መስከረም 13/2018(ኢዜአ)፦ የካፈቾ የአዲስ ዘመን መለወጫ በዓል "ማሽቃሮ" በቦንጋ ከተማ በተለያዩ ባህላዊ ክዋኔዎች በመከበር ላይ ነው።
የ"ማሽቃሮ" በዓል የተራራቀ ወዳጅ ዘመድ የሚገናኝበት፣ የሚጠያየቅበት፤ የተጣላ የሚታረቅበት እንዲሁም መጪው ዘመን የሰላምና የደስታ እንዲሁም የተትረፈረፈ የምርት ዘመን እንዲሆን የምረቃ ስነ ስርዓትም ይከናወናል።
"ማሽቃሮ" በጉጉት የሚጠበቅ ባህላዊና ታሪካዊ በዓል ሲሆን ባህላዊ ጭፈራዎች፣ ፌስቲቫሎች፣ የባህል ምግቦችና መጠጦች የተሰናዱበት ኤግዚቢሽንም ተዘጋጅቷል።
በትውልድ ቅብብሎሽ ባህላዊና ታሪካዊ እሴቱን ጠብቆ በየአመቱ የሚከበረው "ማሽቃሮ" ዘንድሮም የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች እንዲሁም የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍል ተወካዮች በተገኙበት እየተከበረ ይገኛል።