በ20ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የተሳተፈው የኢትዮጵያ ልዑክ አዲስ አበባ ገባ - ኢዜአ አማርኛ
በ20ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የተሳተፈው የኢትዮጵያ ልዑክ አዲስ አበባ ገባ
አዲስ አበባ፤ መስከረም 13/2018(ኢዜአ)፡- በ20ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የተሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ አዲስ አበባ ገብቷል።
በጃፓን ቶኪዮ በተካሄደው 20ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ የተሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካን ጨምሮ ሌሎች አመራሮች አቀባበል አድርገውለታል።