ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በስኬት መጠናቀቁን ተከትሎ በሲዳማ ክልል ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው - ኢዜአ አማርኛ
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በስኬት መጠናቀቁን ተከትሎ በሲዳማ ክልል ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው
ሀዋሳ፤ መስከረም 13/2018(ኢዜአ)፦ በ"ህብረት ችለናል" በሚል መሪ ሀሳብ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ በስኬት መጠናቀቁን ተከትሎ በሲዳማ ክልል አቀፍ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ በሀዋሳ ከተማ እየተካሄደ ነው ይገኛል ።
የድጋፍ ሰልፉ የክልሉ ርዕሰ መተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ነው እየተካሄደ የሚገኘው ።
ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምሮ ከክልሉ ከተለያዩ አካበቢዎች ወደ ሀዋሳ ሚሊኒየም አደባባይ የተመሙ ነዋሪዎች በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ መጠናቀቅ የተሰማቸውን ደስታ በዜማና ቤሎች መርሃ ግብሮች እየገለጹ ይገኛሉ።
ሰልፈኞቹ "ታላቁ የሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅ የብልፅግናችን ምልክት ነው" ፣ "በህብረት ችለናል" ፣ "ግድቡን በስኬት ማጠናቀቅ የድል ሽልማታችን ነው" ፣ "ግድባችን የህብረብሔራዊነታችንና የአንድነታችን መሠረት ነው" ፣ "የህዳሴ ግድብ የኢትዮጵያ ማንሰራራት ምልክት ነው" የሚሉና ሌሎች መልዕክቶችን እያስተላለፉ ይገኛሉ።
የሕዳሴ ግድብ ግንባታ ሂደት በተለያዩ ጫናዎችና ፈተናዎች አልፎ ጳጉሜን 4 ቀን 2017 ዓም በይፋ መመረቁ የሚታወስ ነው።