ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በራስ አቅም ሰርተን ለዓለም ህዝብ ያሳየነው ስኬታችን ነው - የሐረሪ ክልል ነዋሪዎች - ኢዜአ አማርኛ
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በራስ አቅም ሰርተን ለዓለም ህዝብ ያሳየነው ስኬታችን ነው - የሐረሪ ክልል ነዋሪዎች
ሐረር፤ መስከረም 12/2018 (ኢዜአ)፦ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በራስ አቅም ሰርተን ለዓለም ህዝብ ያሳየነው ስኬታችን ነው ሲሉ የሐረሪ ክልል ነዋሪዎች ተናገሩ።
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቁን አስመልክቶ "በህብረት ችለናል" በሚል መሪ ሃሳብ በሐረሪ ክልል ታላቅ የድጋፍ ሰልፍ ተካሂዷል።
በድጋፍ ሰልፉ ላይ የተገኙ ነዋሪዎች ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በይቻላል መንፈስ ሰርተን ለዓለም ህዝብ ያሳየነው የድል ውጤታችን ነው ብለዋል።
ከተሳታፊዎቹ መካከል ሲስተር ፈሪዳ ቡራኔ የህዳሴ ግድብ መጠናቀቅ ኢትዮጵያውያን በይቻላልና በአብሮነት መፈጸም እንደምንችል ያሳየንበትና ለቀጣይም ከመንግስት ጎን በመሆን ተሳትፏችንን እንድናጎለብት መነሳሳት የፈጠረልን ነው ሲሉ ገልጸዋል።
"ግድቡ በራስ አቅም የተገነባ የአፍሪካ ኩራት ነው" ያሉት አቶ በረከት ጸጋዬ ደግሞ በተለይም ግድቡ ሌሎች መሰል የልማት ፕሮጀክቶችን እንድንሰራ አነሳስቶናል ብለዋል።
ወይዘሮ አዳነች ገብሬ በበኩላቸው የህዳሴው ግድብ መመረቅ በራስ አቅምና በጋራ መስራት እንደምንችል ያሳየንበት እንዲሁም አይችሉም ሲሉ ለነበሩት አካላት መፈጸም እንደምንችል ያሳየንበት ነው ብለዋል።
የግድቡ መጠናቀቅ እንዳስደሰታቸውና ለቀጣይ የልማት ስራዎችም መነሳሳትን ፈጥሮልናል ሲሉም ተናግረዋል።
ታላቁ የህዳሴ ግድብ ጀምረን መጨረስ እንደምንችል ያሳየንበትና ጠላቶቻችንን ያሳፈርንበት የስኬት ተምሳሌት ነው ያለው ደግሞ ወጣት አብዱልሃሚድ ረመዳን ነው።