ቀጥታ፡

የሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያን ልጆች ለልማት ያስተባበረ፣ የመደመር ዕሳቤ የታተመበት ፕሮጀክት ነው

 

አዲስ አበባ፤ መስከረም 12/2018(ኢዜአ)፦ የሕዳሴ ግድብ ከጫፍ እስከ ጫፍ በሁሉም የኢትዮጵያ ማዕዘናት የኢትዮጵያ ልጆችን ለልማት ያስተባበረ፣ የመደመር ዕሳቤ የታተመበት ፕሮጀክት ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ከተለያዩ የኢትዮጵያ ተራሮች በሸለቆ እና በሜዳ ገሰግሶ እንደሚገናኘው ታላቁ ዓባይ የብዝሃነት ቤት በሆነችው ድሬዳዋ የሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅን ተከትሎ ዛሬ የድጋፍ ሰልፍ ተደርጓል ብለዋል፡፡


 

የሕዳሴ ግድብ ከጫፍ እስከ ጫፍ በሁሉም የኢትዮጵያ ማዕዘናት የኢትዮጵያ ልጆችን ለልማት ያስተባበረ፣ የመደመር ዕሳቤ የታተመበት ፕሮጀክት ነው ሲሉም ገልጸዋል።


 

በሕዳሴ ግድብ ያየናቸው በፈተናዎች መካከል እንደ አለት ጸንቶ በመቆም ማሸነፍ በደሬዳዋ ያሉ የልማት አቅሞችን ለሀገር ልማት ለማዋል ብርታት ይፈጥራል ብለዋል፡፡


 

ድሬዳዋ የሰላም እና የፍቅር ብቻ ሳይሆን ልማት እና ለለውጥ መበርታትም መገለጫዋ ነው ሲሉም ገልጸዋል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባስተላለፉት መልዕክት።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም