ቀጥታ፡

ታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ መጠናቀቁን አስመልክቶ የድጋፍ ሰልፍ በሐረሪ ክልል እየተካሄደ ነው

ሐረር ፤ መስከረም 12 /2018 (ኢዜአ) "በህብረት ችለናል" በሚል መሪ ሃሳብ ታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ መጠናቀቁን አስመልክቶ  የደስታ መግለጫ የድጋፍ ሰልፍ በሐረሪ ክልል በመካሄድ ላይ ይገኛል።


 

እየተካሄደ በሚገኘው የድጋፍ ሰልፍ ላይም የክልሉ ከፍተኛ አመራሮችና በገጠርና ከተማ ወረዳዎች የሚገኙ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እየተሳተፉ ናቸው።

በህዝባዊ ሰልፉ ላይ፡-

'የህዳሴው ግድብ የኢትዮጵያ ማንሰራራት ምልክት!

የህዳሴው ግድብ የብልፅግናችን አሻራ!

ግድባችን የመቻል ማሳያ የማንሰራራት ጅማሮ ምልክት!

ግድባችን በራሳችን አቅም የገነባነው የአንድነታችንና የአብሮነታችን ምሰሶ!


 

ግድባችን የህብረ ብሔራዊነታችንና የአንድነታችን መሰረት፤ የሚሉና ሌሎች መልዕክቶችን ያዘሉ መፈክሮች በመሰማት ላይ ይገኛሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም