ቀጥታ፡

በሴቶች ከ20 ዓመት በታች የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ኢትዮጵያ እና ኬንያ አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 11/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት ሴቶች ብሄራዊ ቡድን ከኬንያ ጋር ያደረገው የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ አንድ አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቋል። 
  
በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ኤልሳቤት ሚዴቫ ልዋንጉ ጨዋታው በተጀመረ በአንደኛው ደቂቃ ባስቆጠረችው ግብ ኬንያ መሪ ሆናለች።

ከእረፍት መልስ የፊት መስመር ተሰላፊዋ እሙሽ ዳንኤል በ68ኛው ደቂቃ ከመረብ ላይ ያሳረፈችው ጎል ኢትዮጵያን አቻ አድርጓል።

ብሄራዊ ቡድኑ የመልስ ጨዋታውን መስከረም 18 ቀን 2018 ዓ.ም በናይሮቢ ያደርጋል።

ሉሲዎቹ በደርሶ መልስ ውጤት ካሸነፉ በሶስተኛው ዙር ከታንዛንያና አንጎላ አሸናፊ ጋር ይጫወታሉ።

12ኛው የሴቶች ከ20 ዓመት በታች የዓለም ዋንጫ እ.እ.አ በ2026 በፖላንድ አስተናጋጅነት የሚካሄድ ሲሆን 24 ሀገራት ይሳተፋሉ። አፍሪካ በውድድሩ ላይ አራት ሃገራትን ታሳትፋለች።

የአፍሪካ ሀገራት በዓለም ዋንጫው ላይ ለመሳተፍ የማጣሪያ ጨዋታቸውን እያደረጉ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም