ኢትዮጵያ በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮናው አራት ሜዳሊያዎችን በማግኘት አጠናቀቀች - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮናው አራት ሜዳሊያዎችን በማግኘት አጠናቀቀች
አዲስ አበባ፤ መስከረም 11/2018 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ በጃፓን ቶኪዮ በተካሄደው 20ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ሁለት የብር እና ሁለት ነሐስ በድምሩ አራት ሜዳሊያዎችን በማግኘት ውድድሯን አጠናቃለች።
ከመስከረም 3 ቀን 2018 ዓ.ም አንስቶ ሲካሄድ የቆየው ውድድር ዛሬ ፍጻሜውን አግኝቷል።
በሻምፒዮናው ላይ 200 ገደማ ሀገራት የተወጣጡ ከ2000 በላይ አትሌቶች በ49 የውድድር ዓይነቶች ተሳትፈዋል።
ኢትዮጵያ በሻምፒዮናው ባደረገችው ተሳትፎ ሁለት የብር እና ሁለት ነሐስ በድምሩ አራት ሜዳሊያዎችን በማግኘት ውድድሯን አጠናቃለች።
አትሌት ትዕግስት አሰፋ በሴቶች ማራቶን እና አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ በ10000 ሜትር ወንዶች የብር ሜዳሊያ ለኢትዮጵያ አስገኝተዋል።አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ በ10000 ሜትር ሴቶች እና ሲምቦ አለማየሁ በሴቶች 3000 ሜትር መሰናክል የነሐስ ሜዳሊያ ያስገኙ አትሌቶች ናቸው።
በሻምፒዮናው ላይ የተሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑካን ቡድን ነገ ማለዳ አዲስ አበባ እንደሚገባ የባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።