አርሰናል እና ማንችስተር ሲቲ የሚያደርጉት የሳምንቱ ተጠባቂ መርሃ ግብር - ኢዜአ አማርኛ
አርሰናል እና ማንችስተር ሲቲ የሚያደርጉት የሳምንቱ ተጠባቂ መርሃ ግብር
አዲስ አበባ ፤ መስከረም 11/2018 (ኢዜአ):- በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የአምስተኛ ሳምንት መርሃ ግብር አርሰናል እና ማንችስተር ሲቲ ዛሬ የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው።
የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ ከምሽቱ 12 ሰዓት ከ30 ሰዓት ላይ በኤምሬትስ ስታዲየም ይካሄዳል።
በሊጉ አርሰናል በዘጠኝ ነጥብ ሁለተኛ፣ ማንችስተር ሲቲ በስድስት ነጥብ ስምንተኛ ደረጃን ይዟል።
ክለቦች እስከ አሁን በሁሉም ውድድሮች 213 ጊዜ ተገናኝተዋል። አርሰናል 100 ጊዜ በማሸነፍ የበላይነቱን ይዟል። ማንችስተር ሲቲ 65 ጊዜ ድል ቀንቶታል። 48 ጊዜ ደግሞ አቻ ተለያይተዋል።
በጨዋታዎቹ 598 ግቦች ከመረብ ላይ አርፈዋል።
አርሰናል እና ማንችስተር ሲቲ ከዚህ ቀደም በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 51 ጊዜ ተገናኝተዋል። አርሰናል 24 ጊዜ ሲያሸንፍ ማንችስተር ሲቲ 17 ጊዜ ድል ቀንቶታል።10 ጊዜ ደግሞ ነጥብ ተጋርተዋል።
አርሰናል በጨዋታዎቹ 76 ጎሎችን ሲያስቆጥር ማንችስተር ሲቲ 65 ጎሎችን ከመረብ ላይ አሳርፏል።
ሁለቱ ቡድኖች በቅርብ ዓመታት ዋንጫ ለማንሳት እያደረጉት ያለው ፉክክር ጨዋታቸውን ይበልጥ ተጠባቂ ያደርገዋል።
የ42 ዓመቱ ስቱዋርት አትዌል ተጠባቂውን ጨዋታ በዋና ዳኝነት ይመሩታል።
ሰንደርላንድ ከአስቶንቪላ፣ ቦርንማውዝ ከኒውካስትል ዩናይትድ እሁድ በተመሳሳይ 10 ሰዓት የሚደረጉ ሌሎች የሊጉ መርሃ ግብሮች ናቸው።