የሕዳሴ ግድብ ግንባታ በስኬት መጠናቀቅን በማስመልከት ሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ በሠመራ ከተማ እየተካሄደ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የሕዳሴ ግድብ ግንባታ በስኬት መጠናቀቅን በማስመልከት ሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ በሠመራ ከተማ እየተካሄደ ነው
ሠመራ፤ መስከረም 11/2018(ኢዜአ)፦ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በስኬት መጠናቀቅን በማስመልከት በአፋር ክልል ሠመራ ከተማ ሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ይገኛል።
የድጋፍ ሰልፉ ተሳታፊዎች ዛሬ ከማለዳ ጀምሮ ወደ አደባባይ በመውጣት የተለያዩ መልዕክቶችን እያሰሙ ይገኛሉ።
ሰልፈኞቹ የሕዳሴ ግድብ የብልፅግናችን አሻራ ነው፣ ግድባችን የህብረ ብሄራዊነታችንና የአንድነታችን መሠረት ነው፣ የግድቡ ስኬት በሌሎች ፕሮጀክቶች ይደገማል የሚሉና ሌሎችንም መፈክሮች በማሰማት ላይ ናቸው።
የድጋፍ ሰልፉ ላለፉት ቀናት በክልሉ በሚገኙ የተለያዮ ወረዳዎች ሲካሄድ የቆየ ሲሆን ዛሬ ደግሞ በክልል ደረጃ በሰመራ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል።
በሰልፉ ላይ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የመሬት አስተዳደር ቢሮ ኀላፊ አቶ ኡመር ኑርና የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፣ የመንግስት ሰራተኞችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።