በተጠባቂው ጨዋታ ማንችስተር ዩናይትድ ቼልሲን አሸነፈ - ኢዜአ አማርኛ
በተጠባቂው ጨዋታ ማንችስተር ዩናይትድ ቼልሲን አሸነፈ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 10/2018 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የአምስተኛ ሳምንት መርሃ ግብር ማንችስተር ዩናይትድ ቼልሲን 2 ለ 1 አሸንፏል።
ማምሻውን በኦልድትራፎርድ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ብሩኖ ፈርናንዴዝ እና ካሲሚሮ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ናትናኤል ቻሎባህ ለቼልሲ ብቸኛዋን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።
ካሲሚሮ ከማንችስተር ዩናይትድ፣ ሮበርት ሳንቼዝ ከቼልሲ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብተዋል።
በሊጉ ሁለተኛ ድሉን ያስመዘገበው ማንችስተር ዩናይትድ በሰባት ነጥብ 9ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
በውድድር ዓመቱ የመጀመሪያ ሽንፈቱን ያስተናገደው ቼልሲ በስምንት ነጥብ ስድስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።