ቀጥታ፡

በካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ ማጣሪያ ኢትዮጵያ መድን ምላንዴግን አሸነፈ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 10/2018(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ መድን በካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ የመጀመሪያ የማጣሪያ ጨዋታ ኢትዮጵያ መድን የዛንዚባሩን ምላንዴግን 2 ለ 0 አሸንፏል።

በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ አማኑኤል ኤርቦ እና ብሩክ ሙሉጌታ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

ውጤቱ ኢትዮጵያ መድን ወደ ቀጣዩ ዙር የማለፍ እድሉን አስፍቷል።

ኢትዮጵያ መድን እና ምላንዴጌ ኤፍሲ የመልስ ጨዋታቸውን መስከረም 17 ቀን 2018 ዛንዚባር ላይ ያደርጋሉ።

መድን በደርሶ መልስ ውጤት ካሸነፈ በመጨረሻው ዙር ከሩዋንዳው ኤፒአር እና ከግብጹ ኤፍሲ ፒራሚድስ አሸናፊ ጋር ይጫወታል።

ኢትዮጵያ መድን በካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ ኢትዮጵያን ወክሎ የሚወዳደረው የ2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አሸናፊ በመሆኑ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም