ቀጥታ፡

በመርሲሳይድ ደርቢ ሊቨርፑል ኤቨርተንን በማሸነፍ የሊጉን መሪነት አጠናክሯል

አዲስ አበባ፤ መስከረም 10/2018 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የአምስተኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ ሊቨርፑል ኤቨርተንን 2 ለ 1 አሸንፏል።

በአንፊልድ ሮድ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ራያን ግራቨንበርች እና ሁጌ ኢኪቲኬ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

ኢድሪሳ ጌይ ለኤቨርተን ብቸኛዋን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።

ውጤቱን ተከትሎ ሊቨርፑል በ15 ነጥብ የሊጉን መሪነት አጠናክሯል።

ኤቨርተን በሰባት ነጥብ ሰባተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም