በመንግስት ከፍተኛ ጥረት፣ በሁላችንም ትብብርና ተሳትፎ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ለስኬት በመብቃቱ ተደስተናል - ኢዜአ አማርኛ
በመንግስት ከፍተኛ ጥረት፣ በሁላችንም ትብብርና ተሳትፎ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ለስኬት በመብቃቱ ተደስተናል
ሆሳዕና፤ መስከረም 10/2018(ኢዜአ)፡- በመንግስት ከፍተኛ ጥረት፣ በሁላችንም ትብብርና ተሳትፎ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ለስኬት በመብቃቱ ተደስተናል ሲሉ በሆስአና ከተማ የድጋፍ ሰልፍ ታዳሚዎች ተናገሩ።
የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ መጠናቀቅን ተከትሎ "በሕብረት ችለናል" በሚል መሪ ሃሳብ በሆሳዕና ከተማ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ተካሂዷል።
በሰላማዊ ሰልፉ ላይ በመገኘት ኢዜአ ያነጋገራቸው ታዳሚዎች በመንግስት ከፍተኛ ጥረት፣ በሁላችንም ትብብርና ተሳትፎ ግድቡ ለስኬት በመብቃቱ ተደስተናል ብለዋል።
ከሰልፉ ተሳታፊዎቹ መካከል አቶ ሰላሙ ደነቀ እና ወጣት አንጨቴ አድሴ የግድቡ ግንባታ ተጠናቆ በመመረቁ ደስታችንን ለመግለጽ ወደ አደባባይ ወጥተናል ብለዋል።
በግንባታው ሂደት የመንግስት በሳል አመራርና የዲፕሎማሲ ጥረት እንዲሁም የህዝቡ ጠንካራ ትብብርና ተሳትፎ አስደናቂ እንደነበር አስታውሰው ለመሰል የልማት ስራዎች ትብብሩ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አንስተዋል።
በመንግስት ከፍተኛ ጥረት፣ በሁላችንም ትብብርና ተሳትፎ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ለስኬት በመብቃቱ የላቀ ደስታ ተሰምቶናል ብለዋል።
የሃድያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማትዮስ አንዮ፤ ታላቁ ህዳሴ ግድብ የአብሮነታችን ማሳያ የስኬታችን መገለጫ ነው ሲሉ ተናግረዋል።
በኢትዮጵያውያን ብርቱ ጥረት፣ በራስ ሃብትና ጉልበት የተገነባ በመሆኑ ሁላችንም አንኳን ደስ ያለን የሚል መልእክት አስተላልፈዋል።
በመርሃ ግብሩ ላይ የክልሉ ርእሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) እና ሌሎችም የስራ ሃላፊዎችና በከተማዋና አካባቢው የሚገኙ ነዋሪዎች ተሳትፈዋል።