ቀጥታ፡

የሕዳሴ ግድብ ግንባታ በስኬት መጠናቀቅን በማስመልከት ሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ በሆሳዕና ከተማ እየተካሄደ ነው

ሆሳዕና፤ መስከረም10/2018 (ኢዜአ)፦ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በስኬት መጠናቀቅን በማስመልከት በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሆሳዕና ከተማ ሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።

የድጋፍ ሰልፉ ተሳታፊዎች ዛሬ ከማለዳ ጀምሮ ወደ አደባባይ በመውጣት የተለያዩ መልዕክቶችን እያሰሙ ይገኛሉ።


 

“ግድቡ የኛ ነው”፣ “ግድባችን የይቻላል መንፈስ እርሾ የቁጭት ታሪካችን ማብሰሪያ”፣ “ግድቡ የኔ ያንቺ የናንተ ነው”፣”ግድባችን ተጠናቋል የጠላቶቻችን ሴራ በኢትዮጵያዊ አርበኝነት እሳት ተቃጥሎ ከስሟል”፣ የሚሉና ሌሎች በርከታ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም