ቀጥታ፡

በ20ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የ20 ኪሎ ሜትር የርምጃ ውድድር ፍጻሜን የስፔን እና የብራዚል አትሌቶች አሸነፉ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 10/2018 (ኢዜአ)፦ በ20ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የ20 ኪሎ ሜትር የርምጃ ውድድር ፍጻሜን የስፔን እና የብራዚል አትሌቶች አሸንፈዋል።


 

በ20ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የሴቶች የ20 ኪሎ ሜትር የርምጃ ውድድር ፍጻሜ  የስፔኗ አትሌት ማሪያ ፔሬዝ አሸንፋለች።

አትሌቷ ውድድሩን ለማጠናቀቅ 1 ሰዓት ከ25 ደቂቃ ከ54 ሴኮንድ ፈጅቶባታል።

ማሪያ እ.አ.አ በ2019 በሀንጋሪ ቡዳፔስት በተካሄደው 19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በተመሳሳይ ርቀት አሸናፊ እንደነበረች የሚታወስ ነው። አትሌቷ የቡዳፔስት ወርቋን በቶኪዮ ደግማለች።

የሜክሲኮዋ አትሌት አሌና ጎንዛሌዝ 1 ሰዓት ከ26 ደቂቃ ከ06 ሴኮንድ፣ ጃፓናዊቷ  አትሌት ናናኮ ፉጂ   1 ሰዓት ከ26 ደቂቃ ከ18 ሴኮንድ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀዋል።

ኢትዮጵያን ወክላ የተወዳደረችው ስንታየሁ ማስሬ አምስት ኪሎ ሜትር ላይ ውድድሩን አቋርጣለች።


 

በተመሳሳይ የወንዶች የ20 ኪሎ ሜትር የርምጃ ውድድር ፍጻሜ  የብራዚሉ ካዮ ቦንፊ 1 ሰዓት ከ18 ደቂቃ ከ35 ሴኮንድ አሸንፏል።

በወንዶች ቻይናዊው ዣኦዣኦ ዋንግ 1 ሰዓት ከ18 ደቂቃ ከ43 ሴኮንድ ሁለተኛ፣ ስፔናዊው ፖል ማክግራዝ 1 ሰዓት ከ18 ደቂቃ ከ45 ሴኮንድ ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ ውድድራቸውን አጠናቀዋል።

ኢትዮጵያን ወክሎ የተወዳደረው ምስጋና ዋቁማ 1 ሰዓት ከ21 ደቂቃ ከ17 ሴኮንድ 18ኛ ወጥቷል።

ከሌሊቱ 9 ሰዓት ከ55 ላይ በተካሄደው የወንዶች የ20 ኪሎ ሜትር ርምጃ ውድድር ፍጻሜ ፍጻሜ  የብራዚሉ ካዮ ቦንፊም 1 ሰዓት ከ18 ደቂቃ ከ35 ሴኮንድ አንደኛ ወጥቷል።

ቻይናዊው ዣኦዣኦ ዋንግ 1 ሰዓት ከ18 ደቂቃ ከ43 ሴኮንድ ሁለተኛ፣ ስፔናዊው ፖል ማክግራዝ 1 ሰዓት ከ18 ደቂቃ ከ45 ሴኮንድ ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ ውድድራቸውን አጠናቀዋል።

ኢትዮጵያን ወክሎ የተወዳደረው ምስጋና ዋቁማ 1 ሰዓት ከ21 ደቂቃ ከ17 ሴኮንድ 18ኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን አጠናቋል።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም