ቀጥታ፡

ኢትዮ-ሰርት ከአፍሪካ፣ በመካከለኛው ምስራቅና የሙስሊም ትብብር ድርጅት አባል ሀገራት መካከል በተካሄደ የሳይበር መከላከልና ማጥቃት አቅም አሽናፊ ሆነ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 9/2018 (ኢዜአ):- በኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር የሳይበር አደጋ ዝግጁነትና ምላሽ መስጫ ማዕከል ከአፍሪካ፣ መካከለኛው ምስራቅ እንዲሁም ከሙስሊም ትብብር ድርጅት አባል ሀገራት ከተሳተፉበት የሳይበር መከላከልና ማጥቃት ውድድር አሸናፊ መሆኑ ተገለጸ።

ኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር ለኢዜአ በላከው መግለጫ ለአምስት ቀናት በሞሮኮ ራባት በተከናወነው የሳይበር ደህንነት ሳምንትን ተያይዞ በተከናወነ ውድድር ከተለያዩ ሀገራት የተውጣጡ የሳይበር መከላከል ላይ የሚሰሩ ተቋማት ተሳትፈዋል።

በተከናወነው ውድድር ከ30 በላይ ከሙስሊም ትብብር ድርጅት፣ ከአፍሪካና ከመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት የተውጣጡ የሳይበር መከላከል ማዕከላት መሳተፋቸውም ተገልጿል።

ተቋማቱ ባደረጉት የሳይበር መከላከልና ማጥቃት ውድድር የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር ኢትዮጵያን በመወከል በአንደኝነት ማጠናቀቁን ጠቅሷል።

የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር በሳይበር አደጋ ዝግጁነትና ምላሽ መስጫ ማዕከል አማካኝነት የሀገራችንን የዲጂታል ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ 24/7 በተጠንቀቅ የሚሰራና የሀገራችንን የሳይበር ምህዳር የሚጠብቅ ተቋም ነው።

የተገኘው ውጤትም ለቀጣይ ስራዎች መነሳሳትን የሚፈጥር መሆኑን አስታውቋል።

ከኢትዮጵያ በመቀጠል የካዛኪስታን የሳይበር አደጋ ዝግጁነትና ምላሽ መስጫ ማዕከል፣ የፓኪስታን ብሔራዊ የሳይበር ወንጀል ምርመራ ኤጀንሲ፣ ኤል ዋይ እንዲሁም የግብጽ የፋይናንሺያል የሳይበር ክስተት ምላሽ ቡድን ከሁለተኛ እስከ አምስተኛ ያለውን ደረጃ ይዘው ማጠናቀቃቸውም ተጠቅሷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም