ወላይታ ድቻ እና አል-ኢትሃድ ነጥብ ተጋርተዋል - ኢዜአ አማርኛ
ወላይታ ድቻ እና አል-ኢትሃድ ነጥብ ተጋርተዋል

አዲስ አበባ፤ መስከረም 9/2018 (ኢዜአ)፦ ወላይታ ድቻ 2025/26 የካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የመጀመሪያ ማጣሪያ ጨዋታ ከሊቢያው አል-ኢትሃድ ጋር ያደረገው ጨዋታ ያለ ግብ በአቻ ውጤት ተጠናቋል።
ጨዋታው በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ተካሂዷል።
ወላይታ ድቻ እና አል-ኢትሃድ የመልስ ጨዋታቸውን መስከረም 16 ቀን 2018 ዓ.ም ያደርጋሉ። ቡድኑ በደርሶ መልስ ውጤት ካሸነፈ በመጨረሻው ዙር ከግብጹ አል ማስሪ ጋር ይገናኛል።
ወላይታ ድቻ በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ኢትዮጵያን ወክሎ የሚሳተፈው የኢትዮጵያ ዋንጫ አሸናፊ መሆኑን ተከትሎ ነው።