ቀጥታ፡

በሕዳሴ ግድብ የታየው ትዕምርታዊ ተግባር ሕዝቦችን ዋና ተሳታፊና ተጠቃሚ ያደረገ የላቀ የልማት አፈጻጸም ነው -ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 9/2018 (ኢዜአ)፦ በሕዳሴ ግድብ የታየው ትዕምርታዊ ተግባር ሕዝቦችን ዋና ተሳታፊና ተጠቃሚ ያደረገ የላቀ የልማት አፈጻጸም ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።


 

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅን አስመልክቶ ዛሬ የተደረጉ የድጋፍ ሰልፎችን አስመልክቶ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመልዕክታቸውም የተፈጥሮ በረከት የበዛለት፣ የበርካታ ቅመማ ቅመሞች መገኛ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ከሕዳሴ መጠናቀቅ የልማት ጉልበትን ያገኛል ብለዋል።


 

በሕዳሴ ግድብ የታየው ትዕምርታዊ ተግባር ሕዝቦችን ዋና ተሳታፊና ተጠቃሚ ያደረገ የላቀ የልማት አፈጻጸም ነው ሲሉም ገልጸዋል።

በክልሉ የሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅን አስመልክቶ ዛሬ የተደረጉ የድጋፍ ሰልፎች ትናንትን መነሻ በማድረግ እንደሀገር ወደ አለምናቸው የኢትዮጵያ ብልጽግና መዳረሻዎች ለመድረስ የጥንካሬ መንፈስን ይበልጥ የሚያድሱ ናቸው ሲሉም አስፍረዋል፡፡


 

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ህዝቦች በህዝባችን እና መንግስታችን የጋራ ጥረት እንደተሳካው የህዳሴ ግድባችን፣ በቀጣይም ተፈጥሮ ለክልሉ የለገሰቻቸውን እምቅ ፀጋዎች በማልማት ተደማሪ ድሎችን እንደሚቀዳጁ እምነት አለኝ ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም