በ800 ሜትር የሴቶች ማጣሪያ ጽጌ ዱጉማ እና ወርቅነሽ መሰለ ለፍጻሜ ሳያልፉ ቀሩ - ኢዜአ አማርኛ
በ800 ሜትር የሴቶች ማጣሪያ ጽጌ ዱጉማ እና ወርቅነሽ መሰለ ለፍጻሜ ሳያልፉ ቀሩ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 9/2018 (ኢዜአ)፦ በ20ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ ከቀትር በኋላ በተደረገው የ800 ሜትር ሴቶች ማጣሪያ ጽጌ ዱጉማ እና ወርቅነሽ መሰለ ለፍጻሜ ማለፍ አልቻሉም።
በምድብ ሁለት የተወዳደረችው ጽጉ ዱጉማ አምስተኛ፣ በምድብ ሶስት የተወዳደረችው ወርቅነሽ መሰለ ዘጠነኛ ደረጃን በመያዝ ውድድራቸውን አጠናቀዋል።
በሶስት ምድብ በተደረገው ማጣሪያ ከእያንዳንዱ ምድብ አንደኛ እና ሁለተኛ የወጡ አትሌቶች የፊታችን እሁድ ለሚካሄደው የፍጻሜ ውድድር በቀጥታ አልፈዋል።
በተጨማሪም ሁለት ፈጣን ሰዓት ያላቸው ተወዳዳሪዎች ፍጻሜውን ተቀላቅለዋል።