ቀጥታ፡

በሶማሌ ክልል ያለው እምቅ ፀጋ በመደመር እሳቤ ለሀገር እና ለትውልድ አሻራን ለማኖር ትልቅ አቅም መፍጠር የሚችል ነው - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 9/2017(ኢዜአ)፦በሶማሌ ክልል ያለው እምቅ ፀጋ በመደመር እሳቤ ለሀገር እና ለትውልድ አሻራን ለማኖር ትልቅ አቅም መፍጠር የሚችል ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው የስንዴ እና የሩዝ ልማት 'አብዮት' በሚባል ደረጃ በአጭር ጊዜ እየተስፋፋ እና እየለማበት ለሚገኘው የሶማሌ ክልል ሕዝብ የህዳሴ መጠናቀቅ በትጋት ታሪክን መቀየር እንደሚቻል ማሳያ ሆኖለታል ሲሉ አስፍረዋል።


 

በሶማሌ ክልል ያለው እምቅ ፀጋ በመደመር እሳቤ ለሀገር እና ለትውልድ አሻራን ለማኖር ትልቅ አቅም መፍጠር የሚችል ነው ብለዋል።

የሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅን ተከትሎ ዛሬ በክልሉ ያየነው የድጋፍ ሰልፍ በርትቶ ለመስራት፣ ልማትን ለማስቀጠል እና ብልጽግናን ለማረጋገጥ ስንቅ የሚሆን ነው ሲሉም ገልጸዋል፡፡

በክልሉ በተለያዩ ከተሞች የተስተጋቡት መልዕክቶች መንግስትና ሕዝብ ለኢትዮጵያ ማንሠራራትና የከፍታ ጉዞ እጅ ለእጅ ተያይዘው መትመማቸውን በግልፅ ያሳዩ የልማት ቋንቋዎች ናቸው ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም