ቀጥታ፡

የሕዳሴው ግድብ ግንባታ በስኬት መጠናቀቅን በማስመልከት ሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ነው

ቦንጋ፤ መስከረም 9/2018 (ኢዜአ) :- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ  በስኬት መጠናቀቅን በማስመልከት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል  ቦንጋ ከተማ ሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው። 

"በህብረት ችለናል" በሚል መሪ ሃሳብ  እየተካሄደ ባለው በዚህ ክልል  አቀፍ የድጋፍ ሰልፍ ሥነ-ሥርዓት ላይ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር)ን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።


 

ከክልሉ ሁሉም አካባቢዎች የተውጣጡ የሕብረተሰብ  ክፍሎች  በድጋፍ ሰልፉ በመሳተፍ ለይ ይገኛሉ።

የድጋፍ ሰልፉ በክልሉ በሚገኙ ቀበሌዎች፣ ወረዳዎችና በዞን ከተሞች ሲካሄድ ቆይቶ ዛሬ ደግሞ በክልል ደረጃ  በቦንጋ ከተማ አደባባይ በመካሄድ ላይ ነው። 

የሰልፉ ተሳታፊዎች በግድቡ ስኬታማነት  የተሰማቸውን ደስታ  በመግለጽ ግድባችን በራሳችን አቅም የገነባነው የአንድነታችንና የአብሮነታችን ምሰሶ  ነው የሚሉና ሌሎችም ተያያዥ መልዕክቶች በመተላለፍ ላይ ይገኛሉ።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም