ቀጥታ፡

በሻምፒዮንስ ሊጉ ማንችስተር ሲቲ ናፖሊን አሸነፈ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 8/2018 (ኢዜአ)፦ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ መርሃ ግብር ማንችስተር ሲቲ ናፖሊን 2 ለ 0 አሸንፏል።

ማምሻውን በኢትሃድ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ አርሊንግ ሃላንድ በ56ኛው እና ዠረሚ ዶኩ በ65ኛው ደቂቃ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

ሃላንድ በሻምፒዮንስ ሊጉ ያስቆጠራቸውን ግቦች ወደ 50 ከፍ አድርጓል።

የተከላካይ ተጫዋቹን ጆቫኒ ዲ ሎሬንዞ በ21ኛው ደቂቃ በቀይ ካርድ ያጣው ናፖሊ ከ70 ደቂቃ በላይ በ10 ተጫዋቾች ለመጫወት ተገዷል።

በሌሎች ጨዋታዎች ባርሴሎና በማርከስ ራሽፎርድ ሁለት ግቦች ኒውካስትል ዩናይትድን ከሜዳው ውጪ 2 ለ 1 አሸንፏል።

አንቶኒ ጎርደን ለኒውካስትል ዩናይትድ ብቸኛዋን ጎል አስቆጥሯል።

ኢንትራክት ፍራንክፈርት ጋላታሳራይን 5 ለ 1፣ ስፖርቲንግ ሊዝበን ካይራት አልማቲን 4 ለ 1 አሸንፈዋል።

አስቀድመው ዛሬ በተደረጉ ጨዋታዎች ክለብ ብሩዥ ሞናኮን 4 ለ 1 ሲረታ ኮፐንሃገን ከባየር ሌቨርኩሰን ሁለት አቻ ተለያይተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም