የኢትዮጵያ ምድረ ቀደምትነት የምስክር ማህተም በሆነው አፋር ዛሬም የኢትዮጵያ ሰንደቅ በድል ሰልፍ ከፍ ብሎ ውሏል - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ምድረ ቀደምትነት የምስክር ማህተም በሆነው አፋር ዛሬም የኢትዮጵያ ሰንደቅ በድል ሰልፍ ከፍ ብሎ ውሏል - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 8/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ምድረ ቀደምትነት የምስክር ማህተም በሆነው አፋር ዛሬም የኢትዮጵያ ሰንደቅ በድል ሰልፍ ከፍ ብሎ ውሏል ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት የአፋር መሬቱም ሰውም ለሃገር ሉዓላዊነት ዋጋ የከፈለ ጀግና ሆኖ ብቻ አይጠቀስም፤ የልማት ጮራ እየፈነጠቀበት ያለ የልማት አርበኞች ምድር ነው ብለዋል።
የሕዳሴ መጠናቀቅ ለኢትዮጵያ ልማት ለሚተጋው ለአፋር ሕዝብ ተጨማሪ ሃብት እና ወኔ ይሆነዋል ሲሉም ገልጸዋል።
በድጋፍ ሰልፉም የተስተጋባው የአፋር ሕዝብ ድምጽ ለልማት እና ሰላም የወገነ፣ የኢትዮጵያን ብሩህ ዘመን ዕውን ለማድረግ ያለመ እንደሆነ አይተናል ነው ያሉት፡፡