ቀጥታ፡

በ800 ሜትር ሴቶች ማጣሪያ ፅጌ ዱጉማ  እና ወርቅነሽ መሰለ ለግማሽ ፍጻሜ አለፉ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 8/2018 (ኢዜአ)፦ በ 20ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ800 ሜትር ሴቶች ማጣሪያ ፅጌ ዱጉማ እና ወርቅነሽ መሰለ ለግማሽ ፍጻሜ አልፈዋል። 

አትሌት ጽጌ በምድብ አንድ ባደረገችው ውድድር 2 ደቂቃ ከ1 ሴኮንድ ከ53 ማይክሮ ሴኮንድ አንደኛ ወጥታለች። 

በምድብ አምስት የተወዳደረችው ወርቅነሽ መሰለ 1 ደቂቃ ከ58 ሴኮንድ ከ46 ማይክሮ ሴኮንድ  ሶስተኛ ወጥታለች። 

በምድብ ሁለት የተወዳደረችው ንግስት ጌታቸው ስምንተኛ በመውጣት ለግማሽ ፍጻሜ አላለፈችም። 

በሰባት ምድብ ተከፍሎ በተካሄደው ማጣሪያ ከየምድቡ ከአንድ እስከ ሶስት የወጡ አትሌቶች ለግማሽ ፍጻሜ ውድድር በቀጥታ አልፈዋል።

በተጨማሪም ሶስት ፈጣን ሰዓት ያስመዘገቡ አትሌቶች ለግማሽ ፍጻሜ መሳተፋቸውን አረጋግጠዋል። 

የ800 ሜትር ሴቶች የግማሽ ፍጻሜ ውድድር ነገ ከቀኑ 8 ሰዓት ከ45 ላይ ይካሄዳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም