ቀጥታ፡

የትጋትና ውጤታማነት ተምሳሌቶቹ የሀዋሳ ደብረ ምህረት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ትምህርት ቤት ተማሪዎች 

ሀዋሳ ፤ መስከረም 8/2018 (ኢዜአ) :- የትጋትና ውጤታማነት ተምሳሌቶቹ የሀዋሳ ደብረ ምህረት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ትምህርት ቤት ተማሪዎች...

የሀዋሳ ደብረ ምህረት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ትምህርት ቤት ተማሪዎች የሆኑት አርሴማዊት ግሩም፣ አናንያ መንግስቱ እና አንተነህ ማስረሻ በ2017 ዓ.ም በተሰጠው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ  ፈተና የላቀ  ውጤት በማምጣት ለከፍተኛ ትምህርት የተዘጋጁ ተማሪዎች ናቸው።

የግል ትጋታቸውና የመምህራኖቻቸው ጥረት ለውጤት ያበቃቸው መሆኑን ያነሱት ተማሪዎቹ ዓላማ ከተሰነቀ ምንም ነገር ማሳካት ይቻላል ይላሉ። 


 

በፈተናው አርሴማዊት ግሩም እና ተማሪ አናንያ መንግስቱ እያንዳንዳቸው 560 በማምጣት ከፍተኛ ውጤት አስመዝግበው  ለከፍተኛ ትምህርት ተዘጋጅተዋል። 

ሌላኛው የትምህርት ቤቱ ተማሪ አንተነህ ማስረሻ ደግሞ 510 በማምጣት ከትምህርት ቤቱ ከፍተኛ ውጤት ካገኙት መካከል መሆን ችሏል።


 

ተማሪዎቹ በብርታት በማጥናትና የመምህራኖቻችን ልፋት ታክሎበት ለውጤት መብቃት ችለናል፤ በዚህም ተደስተናል ብለዋል።

ከትምህርት ቤቱ መምህራን መካከል መምህር ተስፋሁን እጅጉ፤ በተማሪዎቻችን ውጤት ተደስተናል ፤ በቀጣይም ሌሎች ስኬቶችን ለማስመዝገብ ተዘጋጅተናል ብለዋል።


 

የተማሪዎቹ ውጤትም የግል ጥረታቸው፣  የወላጆች ድጋፍና ክትትል እንዲሁም የመምህራኖች ልፋት ድምር ውጤት መሆኑን ተናግረዋል።

የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር ሀይለኛው ግዛው በበኩላቸው ፤ በትምህርት ቤቱ  ፈተናውን የወሰዱ 68 የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ሁሉም  ለከፍተኛ ትምህርት የማለፊያ ነጥብ በማምጣታቸው ተደስተናል ብለዋል።


 

የተማሪዎቹ ውጤት የወላጆች፣ የመምህራንና አጠቃላይ የትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ እገዛ እንዲሁም የተማሪዎቹ ጥረት ውጤት መሆኑን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም