ቀጥታ፡

በ5000 ሜትር ሴቶች ማጣሪያ ማጣሪያ ጉዳፍ ፀጋይ፣ መዲና ኢሳ እና ፋንታዬ በላይነህ ለፍጻሜ አለፉ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 8/2018 (ኢዜአ)፦ በ20ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ ከቀትር በኋላ በተደረገው የ5000 ሜትር ሴቶች ማጣሪያ ጉዳፍ ፀጋይ፣ መዲና ኢሳ እና ፋንታዬ በላይነህ ለፍጻሜ አልፈዋል። 

በምድብ አንድ  የተወዳደረችው ብርቄ ኃየሎም ዘጠነኛ በመውጣት ለፍጻሜ አላለፈችም። 


 

በሁለት ምድብ ተከፍሎ በተካሄደው ማጣሪያ ከየምድቡ ከአንድ እስከ ስምንት የወጡ አትሌቶች ለፍጻሜ ማለፋቸውን አረጋግጠዋል።

የ5000 ሜትር ሴቶች ፍጻሜ ቅዳሜ መስከረም 10 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 9 ሰዓት ከ29 ላይ ይካሄዳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም