ቀጥታ፡

በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ መርሃ ግብር ተጠባቂ መርሃ ግብሮች ዛሬ ይካሄዳሉ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 8/2018 (ኢዜአ)፦ በ2025/26 የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ዛሬ ስድስት ጨዋታዎች ይደረጋሉ። 

ማንችስተር ሲቲ ከናፖሊ ምሽት 4 ሰዓት ላይ በኢትሃድ ስታዲየም የሚያደርጉት ጨዋታ ትኩረትን ስቧል። 

ሰማያዊዎቹን ለ10 ዓመታት ያገለገለው ቤልጂየማዊው የአማካይ ተጫዋች ኬቨን ደ ብሮይን የቀድሞ ክለቡን ይገጥማል።

በክረምቱ የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ወደ ናፖሊ ያቀናው ደ ብሮይን በኢትሃድ ደማቅ አቀባበል ይደረግለታል ተብሎ ይጠበቃል። 

ኒውካስትል ዩናይትድ ከባርሴሎና፣ ኢንትራክት ፍራንክፈርት ከጋላታሳራይ እና  ስፖርቲንግ ሊዝበን ከካይራት አልማቲ  በተመሳሳይ ምሽት 4 ሰዓት ላይ ይጫወታሉ።

ክለብ ብሩዥ ከሞናኮ እና ኮፐንሃገን ከባየር ሌቨርኩሰን በተመሳሳይ ከምሽቱ 1 ሰዓት ከ45 ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም