በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የወልቂጤ ክላስተር ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው - ኢዜአ አማርኛ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የወልቂጤ ክላስተር ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው

ወልቂጤ፤ መስከረም 8/2018 (ኢዜአ):- በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የወልቂጤ ክላስተር የሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅን በማስመልከት ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።
በድጋፍ ሰልፉ ላይ የተለያዩ መፈክሮችን በማንገብ ከማለዳው ጀምሮ በጎዳናዎችና አደባባዮች ደስታቸውን እየገለጹ ይገኛሉ።
የሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያ ማንሰራራት ምልክት ነው፣ የአባይ ዘመን ትውልድ ተጋድሎ ሰንደቅ ነው፣ የግድቡ ስኬት በሌሎች ፕሮጀክቶችም ይደገማል የሚሉና ሌሎችም መፈክሮችን አንግበዋል።
በሰልፉ ላይ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መሰረተ ልማት ክላስተር አስተባባሪና የትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ኃላፊ መሐመድ ኑርዬ (ዶ/ር) ጨምሮ ሌሎች የክልልና የዞን የስራ ሃላፊዎች፣ የመንግስት ሰራተኞችና የተለያዩ የይብረሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።