ቀጥታ፡

የወቅቱ የአውሮፓ ሻምፒዮናስ ሊግ አሸናፊ ፒኤስጂ ከአትላንታ ጋር የመጀመሪያውን ጨዋታ ያደርጋል

አዲስ አበባ፤ መስከረም 7/2018(ኢዜአ)፦ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የሁለተኛ ቀን ውሎ ዛሬ ስድስት ጨዋታዎች ይደረጋሉ።

የወቅቱ የሻምፒዮንስ ሊግ የዋንጫ ባለቤት ፒኤስጂ ምሽት 4 ሰዓት ላይ በፓርክ ደ ፕራንስ አትላንታን ያስተናግዳል።

ሁለቱ ቡድኖች በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ሲገናኙ የአሁኑ ለሁለተኛ ጊዜ ነው።

እ.አ.አ በ2020 በሩብ ፍጻሜው ተገናኝተው ፒኤስጂ 2 ለ 1 በማሸነፍ ለፍጻሜ ማለፉ የሚታወስ ነው። 

ፒኤስጂ በጨዋታው ከጣልያኑ ክለብ ጠንካራ ፉክክር ይገጥመዋል ተብሎ ይጠበቃል።


 

ሊቨርፑል ከአትሌቲኮ ማድሪድ፣ ባየርሙኒክ ከቼልሲ እና አያክስ ከኢንተር ሚላን በተመሳሳይ ከምሽቱ 4 ሰዓት ላይ የሚያደርጓቸው ጨዋታዎች ተጠባቂ ናቸው። 

ኦሎምፒያኮስ ከፓፎስ ኤፍሲ እና ስላቪያ ፕራግ ከቦዶ ግሊምት በተመሳሳይ ከምሽቱ 1 ሰዓት ከ45 ላይ ይጫወታሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም