ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያውያን አንድነትና አብሮነት ምሰሶ፤ የይቻላል ምልክታችንም ነው - ኢዜአ አማርኛ
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያውያን አንድነትና አብሮነት ምሰሶ፤ የይቻላል ምልክታችንም ነው
መቱ ፤መስከረም 7/2017 (ኢዜአ)፡- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያውያን አንድነትና አብሮነት ምሰሶ፤ የይቻላል ምልክታችንም ነው ሲሉ የመቱ ከተማና ኢሉባቦር ዞን ነዋሪዎች ገለጹ።
የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ መጠናቀቁን አስመልክቶ የድጋፍና የደስታ መግለጫ ሕዝባዊ ሰልፍ በመቱ ከተማ እየተካሄደ ነው።
ግድባችን የጥንካሬያችን ማሳያ የኢትዮጵያ ከፍታ ማብሰሪያም ነው ሲሉም የሰልፉ ተሳታፊዎች ደስታቸውን እየገለጹ ነዉ።
ግድባችን የብዝኃነታችንና የአንድነታችን መሠረት ነው! ግድባችን የሀብታችንና የክብራችን ምልክት ነው!
የሚሉና ሌሎች መልዕክቶችም እየተስተጋቡ ይገኛሉ።
በነገሌ ቦረና፣ አምቦና ጅማ ከተሞች እየተካሄዱ ባሉ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍች ተመሳሳይ መልእክቶች እየተላለፉ ነው።