የታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ መመረቁን በማስመልከት በማያ ከተማ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ መመረቁን በማስመልከት በማያ ከተማ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው
ማያ፤ መስከረም 7/2018 (ኢዜአ)፡- የምስራቅ ሐረርጌ ዞንና የማያ ከተማ ነዋሪዎች የህዳሴ ግድብ መመረቁን አስመልክቶ ታላቅ የድጋፍ ሰልፍ እያካሄዱ ነው።
በድጋፍ ሰልፉ ላይ አርሶ አደሮች፣የከተማና ገጠር ነዋሪዎች፣ወጣቶችና ሴቶች፣ምሁራን፣የመንግስት ሰራተኞች የዞኑና ከተማ መስተዳደሩ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
ሰልፈኞቹም የተለያዩ መልዕክቶችና መፈክሮችን በመያዝና በኅብረት በማሰማት ደስታቸውን በመግለጽ ላይ ይገኛሉ።