ቀጥታ፡

በኦሮሚያ ክልል የሕዳሴ ግድብ መመረቁን አስመልክቶ የድጋፍ ሰልፎች እየተካሄዱ ነው

አዲስ አበባ፤ መስከረም 7/2018(ኢዜአ)፦ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ተጠናቆ መመረቁን በማስመልከት በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማን ጨምሮ በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች ሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፎች እየተካሄዱ ይገኛሉ።


 

‘በኅብረት ችለናል’ በሚል መሪ ሐሳብ እየተካሄደ በሚገኘው የድጋፍ ሰልፍ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች መንግስት የኢትዮጵያን ብልጽግና እውን ለማድረግ ለሚያደርገው ጥረት ያላቸውን አጋርነት እየገለጹ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም