መደመር ተብሎ የተጀመረው የሀገራዊ ዕሳቤ ጉዞ ዛሬ የመደመር መንግሥት ላይ ደርሷል -ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ - ኢዜአ አማርኛ
መደመር ተብሎ የተጀመረው የሀገራዊ ዕሳቤ ጉዞ ዛሬ የመደመር መንግሥት ላይ ደርሷል -ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 6/2018(ኢዜአ)፦ መደመር ተብሎ የተጀመረው የሀገራዊ ዕሳቤ ጉዞ ዛሬ የመደመር መንግሥት ላይ ደርሷል ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተጻፈው 'የመደመር መንግሥት' የተሰኘው መጽሐፍ በዛሬው ዕለት ተመርቋል፡፡
በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የእንኳን ደስ ያለዎት መልዕክት ያስተላለፉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ መደመር ተብሎ የተጀመረው የሀገራዊ ዕሳቤ ጉዞ ዛሬ የመደመር መንግሥት ላይ ደርሷል ሲሉም ገልጸዋል።
በአንድ በኩል እየመሩ፣ እየሠሩ፤ በሌላ በኩል እያጠኑ፣ እየመረመሩ ላበረከቱልን መጽሐፍ እናመሰግናለን ብለዋል።