የ15 ጊዜ የሻምፒዮንስ ሊግ አሸናፊው ሪያል ማድሪድ ማርሴይን በማሸነፍ በድል ጀምሯል - ኢዜአ አማርኛ
የ15 ጊዜ የሻምፒዮንስ ሊግ አሸናፊው ሪያል ማድሪድ ማርሴይን በማሸነፍ በድል ጀምሯል

አዲስ አበባ፤ መስከረም 6/2018 (ኢዜአ)፦ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ መርሃ ግብር ሪያል ማድሪድ ማርሴይን 2 ለ 1 አሸንፏል።
ማምሻውን በሳንቲያጎ በርናባው ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ቲሞቲ ዊሃ በ22ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ጎል ማርሴይን መሪ አድርጓል።
ኪሊያን ምባፔ በ29 እና በ81ኛው ደቂቃ በፍጹም ቅጣት ምት ከመረብ ላይ ባሳረፋቸው ግቦች ሪያል ማድሪድ ባለ ድል ሆኗል።
ምባፔ ለማድሪድ ያስቆጠራቸውን የጎል ብዛት 50 አድርሷል።
የሪያል ማድሪዱ ተከላካይ ዳንኤል ካርቫያል በ72ኛው ደቂቃ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል።
ማድሪድ በጨዋታው የመጀመሪያ አጋማሽ ያገኛቸውን በርካታ ግልጽ የግብ እድሎች አልተጠቀመም።
በሌሎች ጨዋታዎች ጁቬንቱስ እና ቦሩሲያ ዶርትሙንድ አራት አቻ ተለያይተዋል።
ቶተንሃም ሆትስፐርስ ቪያሪያልን 1 ለ 0 እና ካራባግ ቤኔፊካን 3 ለ 2 አሸንፈዋል።