ቀጥታ፡

አርሰናል አትሌቲኮ ቢልባኦን አሸነፈ 

አዲስ አበባ፤ መስከረም 6/2018(ኢዜአ)፦ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ አርሰናል አትሌቲኮ ቢልባኦን 2 ለ 0 በማሸነፍ ጉዞውን በድል ጀምሯል። 

ማምሻውን በሳን ማሜስ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ተቀይረው የገቡት ጋብርኤል ማርቲኔሊ በ72ኛው እና ሊያንድሮ ትሮሳርድ በ87ኛው ደቂቃ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል። 

በጨዋታው አርሰናል በኳስ ቁጥጥር እና ለግብ የቀረቡ ሙከራዎችን በማድረግ ከተጋጣሚው የተሻለ ነበር።

በተመሳሳይ ሰዓት በተካሄደ ጨዋታ ዩኒየን ሴይንት-ጊሎስ ፒኤስቪ አይንድሆቨንን ከሜዳው ውጪ 3 ለ 1 አሸንፏል።

ዛሬ የተጀመረው የ2025/26 የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ማምሻውን ሲቀጥል ሪያል ማድሪድ ከማርሴይ፣ ጁቬንቱስ ከቦሩሲያ ዶርትሙንድ፣ ቶተንሃም ሆትስርስ ከቪያሪያል እና ቤኔፊካ ከካራባግ በተመሳሳይ ከምሽቱ አራት ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም