ኬንያዊቷ አትሌት ፌዝ ኪፕዬጎን በ1 ሺህ 500 ሜትር ሴቶች የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች - ኢዜአ አማርኛ
ኬንያዊቷ አትሌት ፌዝ ኪፕዬጎን በ1 ሺህ 500 ሜትር ሴቶች የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

አዲስ አበባ፤ መስከረም 6/2018 (ኢዜአ)፦ በ20ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በሴቶች 1 ሺህ 500 ሜትር ፍጻሜ ኬንያዊቷ አትሌት ፌዝ ኪፕዬጎን በማሸነፍ የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት ሆናለች።
ኪፕዬጎን ውድድሩን ለማጠናቀቅ 3 ደቂቃ ከ52 ሴኮንድ ከ15 ማይክሮ ሴኮንድ ወስዶባታል።
ኬንያዊቷ አትሌት በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የ1 ሺህ 500 ሜትር ሴቶች አራት የወርቅ ሜዳሊያዎችን ያገኘች የመጀመሪያዋ ሯጭ ሆናለች።
ሌላኛዋ ኬንያዊት አትሌት ዶርከስ ኢዎ ሁለተኛ፣ አውስትራሊያዊቷ ጄሲካ ሁል ሶስተኛ በመውጣት ውድድራቸውን አጠናቀዋል።
ኢትዮጵያን ወክላ የተወዳደረችው አትሌት ፍሬወይኒ ኃይሉ 3 ደቂቃ ከ57 ሴኮንድ ከ33 ማይክሮ ሴኮንድ ስድስተኛ ወጥታለች።
በተያያዘም ዛሬ በ800 ሜትር ወንዶች በተደረገ የመጀመሪያ ዙር ማጣሪያ ኢትዮጵያን ወክሎ የተወዳደረው አትሌት ዮሐንስ ተፈራ ስምንተኛ ወጥቶ ለግማሽ ፍጻሜ ሳያልፍ ቀርቷል።