በአማራ ክልል የተለያዩ ከተሞች የሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅን አስመልክቶ ሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው - ኢዜአ አማርኛ
በአማራ ክልል የተለያዩ ከተሞች የሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅን አስመልክቶ ሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው

ባህርዳር፤ መስከረም 6/2018(ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል ባህር ዳርን ጨምሮ በተለያዩ ከተሞች የሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅን አስመልክቶ ሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።
የድጋፍ ሰልፉ በኅብረት ችለናል! በሚል ሃሳብ በክልሉ ባህር ዳር ከተማን ጨምሮ ጎንደር፣ ደሴ፣ ደብረ ብርሃን፣ ደብረ ማርቆስ፣ ወልድያ፣ ሰቆጣ፣ ደብረ ታቦር፣ እንጅባራ፣ ገንዳ ውሃና ሌሎችም ከተሞች ከማለዳው ጀምሮ እየተካሄደ ይገኛል።
የሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያ ማንሰራራት ምልክት ነው፣ የብልጽግናችን አሻራ፣ የሚጨበጥ ብርሃን ያየንበት ነው፤ በራስ አቅም የተገነባ የሀገር ሃብትና የአፍሪካ ኩራት የሚሉና ሌሎችንም መፈክሮች ሰልፈኞቹ አንግበዋል።
የአባይ ዘመን ትውልድ አኩሪ ገድል የሚዘከርበትና የህብረ ብሔራዊ አንድነታችን መሰረት እንዲሁም የማንሰራራት ጅማሮ ነው የሚሉም እንዲሁ።