የህዳሴ ግድብ ከብርሃን ምንጭነቱ ባለፈ ለዓሳ ሃብትና ለመስህብ ስፍራነት ተመራጭ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የህዳሴ ግድብ ከብርሃን ምንጭነቱ ባለፈ ለዓሳ ሃብትና ለመስህብ ስፍራነት ተመራጭ ነው

ባህር ዳር ፤ መስከረም 5/2018 (ኢዜአ)፦ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ከብርሃን ምንጭነት ባለፈ ለዓሳ ሃብትና ለመስህብ ስፍራነት የሚመረጥ የሀገር ሃብት መሆኑ ተመላከተ።
የአማራ ክልል የአካባቢና ደን ጥበቃ ባለስልጣን ''የህዳሴ ግድብ የኢትዮጵያ የማንሰራራት ምልክት'' በሚል መሪ ሃሳብ ከተለያዩ ተቋማት ጋር የፖናል ውይይት አካሂዷል።
በዚሁ መድረክ ላይ የተገኙት የባለስልጣኑ ኃላፊ አቶ ተስፋሁን አለምነህ፤ የህዳሴ ግድብ ግንባታ በህብረ ብሄራዊ አንድነት፤ በራስ ጥሪትና ጉልበት ተገንብቶ የተጠናቀቀ በመሆኑ ደስታው የጋራችን ሆኗል ብለዋል።
በግንባታው ሂደት የመንግስት ቁርጠኝትና የዲፕሎማሲ ከፍታ የታየበት መሆኑን አንስተው የህዝቡም ጠንካራ ትብብር በተግባር የተገለጠበት መሆኑን ተናግረዋል።
በመሆኑም ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ከብርሃን ምንጭነቱ ባለፈ በዓሳ ሃብትና በመስህብ ስፍራነት የሚመረጥ የሀገር ሃብት መሆኑን አንስተዋል።
የክልሉ ህብረት ስራ ኮሚሽን ምክትል ኃላፊ እንዳልካቸው ሲሳይ በበኩላቸው፤ የግድቡ መጠናቀቅ የኢትዮጵያውያንን የመፈፀም አቅም ያረጋገጠ መሆኑን ገልጸው በቀጣይም ግዙፍ ፕሮጀክቶችን ጀምሮ መጨረስ እንደሚቻል ያሳየ ነው ብለዋል።