ቀጥታ፡

ቻይና ለአፍሪካ ልማትና ዕድገት የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ ትቀጥላለች - አምባሳደር  ጃንግ ፋንግ

አዲስ አበባ ፤ መስከረም 5/2018 (ኢዜአ)፦ቻይና ለአፍሪካ ልማትና እድገት የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል በአፍሪካ ህብረት የቻይና ልዑክ ኃላፊ አምባሳደር ጃንግ ፋንግ ገለጹ። 

በአፍሪካ ህብረት የቻይና ልዑክ ኃላፊ አምባሳደር ጃንግ ፋንግ በተለይ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ፤ ቻይና እና አፍሪካ በቀጣናዊ እና አለምአቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ትብብር አጠናክረው መቀጠላቸውን  ተናግረዋል፡፡

በተለይ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሪፎርም፣ የአየር ንብረት ለውጥ እና ሽብርተኝነትን በመዋጋት ረገድ በጋራ እየሰሩ ስለመሆኑ አብራርተዋል፡፡

ቻይና የአፍሪካን ልማት እና ዕድገት መደገፏን እንደምትቀጥልም ጨምረው ገልፀዋል፡፡

አፍሪካውያን የራሳቸውን ችግሮች በራሳቸው የመፍታት አቅሙ እና ጥበቡ እንዳላቸው ቻይና ታምናለች  ያሉት አምባሳደሩ፤ ቻይና በአፍሪካ ህብረት በኩል የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥልም አረጋግጠዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም