ቀጥታ፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ አዲስ ከተመረጡት ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አመራሮች ጋር ተወያዩ 

አዲስ አበባ፤ መስከረም 5/2018 (ኢዜአ)፦ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ አዲስ ከተመረጡት ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አመራሮች ጋር ዛሬ ተወያይተዋል።



  
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ውይይቱን አስመልክቶ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ሀገር አቀፍ የመጅሊስ ምርጫው በተሳካ መልኩ እንዲካሄድ በማድረጋቸው ለህዝበ ሙስሊሙና ለምክር ቤቱ አመራሮች አድናቆቴን ለመግለጽ እወዳለሁ ብለዋል። 


 

የመጅሊስ ምርጫው ፍጹም ሰላማዊ፣ አካታችና አሳታፊ በሆነ መልኩ መከናወኑ ትምህርት የሚሰጥ መሆኑን ገልጸዋል።  

መንግሥት ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አመራሮች ጋር በጋራ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ይበልጥ ተቀራርቦ የሚሠራ ሲሆን በሚያስፈልገው ሁሉ የሚጠበቅበትን ድጋፍ እንደሚያደርግ አመልክተዋል።  


 

ለምክር ቤቱ አመራሮች መልካም የአገልግሎት ዘመን እንዲሆንላቸው እመኛለሁ ብለዋል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም