ኒውዝላንዳዊው አትሌት ጂኦርዲ ቢሚሽ በወንዶች 3000 ሜትር መሰናክል የወርቅ ሜዳሊያ አገኘ - ኢዜአ አማርኛ
ኒውዝላንዳዊው አትሌት ጂኦርዲ ቢሚሽ በወንዶች 3000 ሜትር መሰናክል የወርቅ ሜዳሊያ አገኘ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 5/2018 (ኢዜአ)፦ በ20ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በወንዶች 3000 ሜትር መሰናክል ፍጻሜ ኒውዝላንዳዊው አትሌት ጂኦርዲ ቢሚሽ አንደኛ በመውጣት የወርቅ ሜዳሊያ አግኝቷል።
ሞሮኮዋዊው አትሌት ሶፊያን ኤል ባካሊ ሁለተኛ፣ ኬንያዊው አትሌት አሞስ ሴሬም ሶስተኛ ደረጃን ይዘዋል።
ኢትዮጵያን ወክለው የተወዳደሩት አትሌት ሳሙኤል ፍሬው አራተኛ፣ አትሌት ለሜቻ ግርማ ስድስተኛ እና ጌትነት ዋለ 14ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀዋል።
በቶኪዮ እየተካሄደ በሚገኘው 20ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ እስከ አሁን ሁለት የብር እና አንድ የነሐስ ሜዳሊያ አግኝታለች።