ቀጥታ፡

በ3000 ሜትር መሰናክል ሴቶች ማጣሪያ  ሲምቦ አለማየሁ እና ሎሚ ሙለታ ለፍጻሜ አለፉ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 5/2018(ኢዜአ)፦ በ20ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ትናንት ከእኩለ ሌሊት በኋላ በተካሄደው የ3000 ሜትር ሴቶች መሰናክል ማጣሪያ ሲምቦ አለማየሁ እና ሎሚ ሙለታ ለፍጻሜ አልፈዋል።

በማጣሪያው ላይ የተሳተፈችው ዓለምናት ዋለ ውድድሩን አቋርጣለች።


 

የማጣሪያ ውድድሩ በሶስት ምድቦች ተከፍሎ የተደረገ ሲሆን ከየምድቡ ከአንድ እስከ አምስት የወጡ አትሌቶች ለፍጻሜ አልፈዋል።

የፍጻሜው ውድድር ረቡዕ መስከረም 7 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 9 ሰዓት ከ57 ላይ ይካሄዳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም