ቀጥታ፡

የታንዛኒያው አልፎንስ ሲምቡ የወንዶች ማራቶን አሸነፈ

አዲስ አበባ፤መስከረም 4/2018(ኢዜአ)፦ በ20ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የወንዶች ማራቶን ታንዛኒዊያው አትሌት አልፎንስ ሲምቡ አሸንፏል።

ሲምቡ 2 ሰዓት ከ9 ደቂቃ ከ48 ሴኮንድ በማሸነፍ በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በማራቶን ለታንዛኒያ የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ አስገኝቷል።

ጀርመናዊው አማኑኤል ጴጥሮስ አንገት ለአንገት ተናንቆ 2 ሰዓት ከ9 ደቂቃ ከ48 ሴኮንድ ከታንዛንያው አትሌት ጋር በተመሳሳይ ሰዓት ቢገባም በፎቶ ፊኒሺንግ ቴክኖሎጂ በሲምቡ በመቀደሙ ሁለተኛ ወጥቷል።


 

ጣልያናዊው ኢሊያስ አኩዋኒ 2 ሰዓት ከ9 ደቂቃ ከ53 ሴኮንድ ሶስተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል።

በውድድሩ ላይ የተሳተፉት አትሌት ታደሰ ታከለ፣ ደረሳ ገለታ እና ተስፋዬ ድሪባ ውድድሩን አቋርጠው ወጥተዋል።

በቶኪዮ እየተካሄደ ባለው 20ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ እስከ አሁን ሁለት የብር እና አንድ የነሐስ ሜዳሊያ አግኝታለች።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም