ቀጥታ፡

በተጠባቂው የደርቢ ጨዋታ ማንችስተር ሲቲ ማንችስተር ዩናይትድን አሸነፈ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 4/2018 (ኢዜአ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የአራተኛ ሳምንት ፕሪሚየር ሊግ ተጠባቂ መርሃ ግብር ማንችስተር ሲቲ ማንችስተር ዩናይትድን 3 አሸንፏል።

ማምሻውን በኢትሃድ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ አርሊንግ ሃላንድ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ፊል ፎደን ቀሪዋን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።

ውጤቱን ተከትሎ ማንችስተር ሲቲ በስድስት ነጥብ ስምንተኛ፣ ማንችስተር ዩናይትድ በአራት ነጥብ 14 ደረጃን ይዘዋል።

በሌላኛው የአራተኛ ሳምንት መርሃ ግብር ሊቨርፑል በርንሌይን መሐመድ ሳላህ 95ኛው ደቂቃ በፍጹም ቅጣት ባስቆጠራት ጎል አሸንፏል።

ድሉን ተከትሎ ሊቨርፑል 12 ነጥብ የሊጉን መሪነት ከአርሰናል ተረክቧል። ቡድኑ በሊጉ አራት ጨዋታዎችን ያሸነፈ ብቸኛው ክለብ ሆኗል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም