ቀጥታ፡

ሊቨርፑል በርንሌይን በማሸነፍ የፕሪሚየር ሊግ መሪነቱን አጠናከረ

አዲስ አበባ፤መስከረም 4/2018 (ኢዜአ)፡-ሊቨርፑል በርንሌይን 1 ለ 0 በማሸነፍ የፕሪሚየር ሊግ መሪነቱን አጠናክሯል።

ሞሐመድ ሳላህ በፍጹም ቅጣት ምት ባስቆጠራት ብቸኛ ግብ በርንሌን የረታው ሊቨርፑል፤በ12 ነጥብ የደረጃ ሠንጠረዡን እየመራ ነው።

ሊቨርፑል እስካሁን በሊጉ ያከናወናቸውን አራቱን ጨዋታዎች ያሸነፈ ብቸኛው ክለብ ነው።

አርሰናል እና ቶተንሃም ሆትስፐር በግብ ክፍያ ተበላልጠው በተመሳሳይ ዘጠኝ ነጥብ ሁለተኛ እና ሦስተኛ ደረጃን ይዘዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም