ቀጥታ፡

በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና 8.4 በመቶ ተማሪዎች 50 በመቶ እና ከዚያ በላይ ውጤት አምጥተዋል -ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ

አዲስ አበባ፤መስከረም 4/2018 (ኢዜአ)፦ በ2017 ዓ.ም ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና 8.4 በመቶ ተማሪዎች 50 በመቶ እና ከዚያ በላይ ውጤት ማስመዝገባቸውን የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ገለጹ፡፡

ሚኒስትሩ የትምህርት ዘመኑን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤትን አስመልክተው መግለጫ እየሰጡ ይገኛሉ፡፡

በ2017 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች 48 ሺህ 929 ተማሪዎች ከ50 በመቶ በላይ ውጤት በማምጣት አልፈዋል።

ይህም ከአምና ከነበረው 36 ሺህ 409 ተማሪዎች ጋር ሲነፃፀር የ12 ሺህ ልዩነት እንዳለው ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም